Search

የተቸነከረው ትውልድ አባል አይደለሁም፡- አቶ ጌታቸው ረዳ

ረቡዕ መስከረም 07, 2018 43

ከመደመር መጻሕፍት የመጀመሪያውን ማንበባቸውን የገለጹት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ፤ በወቅቱ መጽሐፉን ያነበቡት አቃቂር ለማውጣት እንደነበር አክለዋል።

በወቅቱ በወጉ አቃቂር ማውጣት እንኳን አለመቻላቸውን ጠቅሰው፤ በኋላም በነበረው ችግር ሁለቱን የመደመር መጻሕፍት የማንበብ ዕድል እንዳላገኙ አቶ ጌታቸው በመደመር መንግሥት መጽሐፍ ዙሪያ ባቀረቡት ዳሰሳ ተናግረዋል።

በመደመር መንግሥት መጽሐፍ ውስጥ ከተዘረዘሩት አምስቱ ትውልዶች መካከል ቢያንስ የተቸነከረው ትውልድ አባል እንዳልሆንኩ ግን እርግጠኛ ነኝ በማለት አቶ ጌታቸው ታዳሚውን ፈገግ አሰኝተዋል።

በንፍታሌም እንግዳወርቅ

#EBCdotstream #YemedemerMengist #AbiyAhmedAli