Search

ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን አጀንዳ ሊያሰባስብ ነው

ሓሙስ መስከረም 08, 2018 31

ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን መስከረም 10/2018 . በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች ከሚገኙ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማኅበረሰብ አባላት አጀንዳ የሚያሰባስብበትና የሀገራዊ ምክክር ጉባዔ ተሳታፊዎች የሚለይበት መድረክ እንደሚያካሂድ አስታወቀ። 

በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች እና አካባቢው ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን አጀንዳ ለማሰባሰብ ወደ አካባቢው ያቀናው የኮሚሽነሮች ልዑካን ቡድን፤ ከዲያስፖራ አደረጃጀቶች ጋር ተወያይቷል። 

ኮሚሽኑ መስከረም 10/2018 . በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች ከሚገኙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት አጀንዳ የሚያሰባስብበትና የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ተሳታፊዎች የሚለይበት መድረክ እንደሚያካሂድ ለአደረጃጀቶቹ አስታውቋል። 

መድረኩ ሀገራዊ ፋይዳቸው የላቀ አጀንዳዎች የሚሰበሰቡበትና የተሳካ እንዲሆን በአካባቢው የሚገኙ የዳያስፖራ አደረጃጀቶች ኮሚሽኑን እንዲያግዙም ተጠይቋል። 

አደረጃጀቶቹ በምክክር መድረኩ በንቃት እንዲሳተፉ ብሎም በአካባቢው የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንዲገኙ በማስተባበር እንዲያግዙ ነው የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን ዓርዓያ (ፕሮፌሰር) ጥሪ ያቀረቡት።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በተባበሩት አረብ ኤምሬቶችና አካባቢው ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን አጀንዳ የሚያሰባስብበት የምክክር መድረክ በመጪው ቅዳሜ መስከረም 10/2018 ወይም ሴፕቴምበር 20/2025 ከሰዓት በኃላ 300 PM ጀምሮ Jumeirah Creekside Hotel, Al Garhoud Dubai የሚካሄድ ይሆናል።