በዘንድሮው የኢሬቻ በዓል አከባበር ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በቢሾፍቱ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በውይይቱ ላይ አባገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ሙሁራን እና የክልሉ አመራሮች ተገኝተዋል።
የኦሮሚያ ክልል የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ጀሚላ ሲንብሩ በውይይቱ ላይ፤ ኢሬቻ የአብሮነት በዓል ነው ብለዋል፡፡
ኢሬቻ ባህሉን እና ወጉን ጠብቆ እንደ ቀደሞ በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ከፍተኛ ዝግጅት መደረጉንም አንስተዋል፡፡
የዘንድሮ ኢሬቻ በዓል የህዳሴ ግድብ በተጠናቀቀበት ዓመት ላይ የሚከበር በመሆኑም ልዩ እንደሚያደርገው ገልፀዋል፡፡
ኢሬቻ የሚከበሩበት መልካዎች በቁጥር እየጨመሩ በመምጣት 86 ደርሷል ያሉት ኃላፊዋ፤ ይህም የቱሪስት ፍሰት እንዲጨምር ማስቻሉን ተናግረዋል፡፡
በዉይይቱ ላይ ኢሬቻ ከየት ተነስቶ የት ደርሷል በሚል ርዕስ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጓል።
የዘንድሮው ኢሬቻ በዓል "ኢሬቻ ለሀገር ከፍታ" በሚል መሪ ሐሳብ ይከበራል።
በዓሊ ደደፎ
#ebc #ebcdotstream #Ethiopia #Irrecha #Ceremony