የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታን በ2018 ዓ.ም ኅዳር መጨረሻ ለመጀመር እቅድ መያዙን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ገለጹ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የኢትዮጵያን የአቪየሽን ኢንዱስትሪ ወደ ላቀ ምዕራፍ እንደሚያሸጋግረው አስታውቀዋል።
አውሮፕላን ማረፊያው አየር መንገዱ በአፍሪካ የአየር ትራንስፖርት እየተጫወተ ያለውን ግንባር ቀደም ሚና የበለጠ እንደሚያሳድገው አመላክተዋል።
ዋና ሥራ አስፈጻሚው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታን ለመጀመር የሚያስችሉ ዝግጅቶች በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸውንም አንስተዋል።
የግንባታውን የመጀመሪያ ደረጃ ስራ ለማከናወን የኮንትራክተሮች መረጣ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታን በኅዳር ወር መጨረሻ ለመጀመር እቅድ መያዙንም አመላክተዋል።