የኢትዮጵያ ምድረ ቀደምትነት የምስክር ማህተም በሆነው አፋር ዛሬም የኢትዮጵያ ሰንደቅ በድል ሰልፍ ከፍ ብሎ ውሏል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

የአፋር መሬቱም ሰውም ለሃገር ሉዓላዊነት ዋጋ የከፈለ ጀግና ሆኖ ብቻ አይጠቀስም፤ የልማት ጮራ እየፈነጠቀበት ያለ የልማት አርበኞች ምድር ነው ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት።

የሕዳሴ መጠናቀቅ ለኢትዮጵያ ልማት ለሚተጋው ለአፋር ሕዝብ ተጨማሪ ሃብት እና ወኔ ይሆነዋል ሲሉም ነው የገለጹት።
በድጋፍ ሰልፉም የተስተጋባው የአፋር ሕዝብ ድምጽ ለልማት እና ሰላም የወገነ፣ የኢትዮጵያን ብሩህ ዘመን ዕውን ለማድረግ ያለመ እንደሆነ አይተናል ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።