Search

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ 5 አህጉራት መንገደኞችን እያጓጓዘ ነው - አቶ መስፍን ጣሰው

ሓሙስ መስከረም 08, 2018 20

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ2026 ለመንገደኞች የሚያቀርበውን የምግብ አማራጮች የማስተዋወቂያ መርኃ ግብር በስካይላይት ሆቴል አከናውኗል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው በዚሁ ወቅት፤ አየር መንገዱ ወደ 5 አህጉራት መንገደኞችን እያጓጓዘ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የተካሄደው የምግብ ማስተዋወቂያ መርኃ ግብር የደንበኞችን የምግብ ፍላጎት ለማሟላት በተቋሙ ባለሙያዎች መዘጋጀቱን አቶ መስፍን ተናግረዋል።

አየር መንገዱ ዓለም አቀፍ ምርጥ ሼፎችን በመቅጠር ለመንገደኞች እየሰጠ ባለው የምግብ አቅርቦት የአፍሪካ ምርጥ ቢዝነስ ክላስ ኬተሪንግ ሽልማት ማሸነፉንም ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያዘጋጀው የምግብ ማስተዋወቂያ መርኃ ግብር ከደንበኞች ግብዓት ለማግኘትና ለማሻሻል እንደሚረዳው ተገልጿል።

በላሉ ኢታላ

#ebc #ebcdotstream #EthiopianAirlines #Catering