የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) የመደመር መንግሥት መጽሐፍ ሀገርን ማሻገሪያ መንገዶችን ቁልጭ አድርጎ ያሳየ መሆኑን ገልጸዋል።
መጽሐፉ ሶስት ጊዜ መብላት ከሚለው በእጅጉ በላቀ ምናባዊ ከፍታ ተጨባጭ የሆኑ ሕልሞችን እና ሀገርን ማሻገሪያ መንገዶችን ቁልጭ አድርጎ አሳይቷል ብለዋል።
የመንግሥታዊ እና የማህበራዊ አገልግሎቶች ማሻሻያ ላይ የመፍትሔ ሀሳቦችን የያዘ መጽሐፍ መሆኑንም ዶ/ር ፍፁም ተናግረዋል።
መጽሐፉ ፍጥነት፣ ፈጠራ እና ዝላይ በማለት ያመላከታቸውን ሀገር ማሻገሪያ መንገዶች በዝርዝር እንደሚያብራራ አንስተዋል።
የሀገሪቱ የዲጂታል ሽግግር ጉዞ የቴክኖሎጂ መሠረት ልማትን ከማጠናከር እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ከመዘርጋት መጀመር እንዳለበት በመጽሐፉ በግልጽ መቀመጡን ጠቅሰዋል።
ተቋማት የአሠራር ሥርዓቶቻቸውን በቴክኖሎጂ በማዘመን አገልግሎቶችን በኦንላይን እንዲሰጡ እና እርስ በርስ እንዲቀናጁ ማድረግ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
የመደመር መንግሥት እሳቤ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ከከተማ እስከ ገጠር በተለያዩ መስኮች ተተግብሮ በርካታ ተጨባጭ ለውጦች ማምጣቱንም ነው ሚኒስትሯ የገለጹት።
በቢታንያ ሲሳይ
#EBCdotstream #Ethiopia #YemedemerMengist