Search

ኢሬቻ በሆረ ፊንፊኔ መስከረም 24 እና በሆረ ሀርሰዲ መስከረም 25 ይከበራል

ሓሙስ መስከረም 08, 2018 32

የ2018 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል በሆረ ፊንፊኔ መስከረም 24 እና በሆረ ሀርሰዲ (ቢሾፍቱ) መስከረም 25 እንደሚከበር ተገልጿል።

የኦሮሞ አባገዳዎች ኅብረት የበዓሉን አከባበር አስመልክቶ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥቷል።

ኅብረቱ በመግለጫው፥ የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል ዳግማዊ ዓድዋ የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታው በመላው ኢትዮጵያውያን ኅብረት በስኬት ተጠናቅቆ በተመረቀ ማግስት የሚከበር በመሆኑ ደስታችን እጥፍ ድርብ ነው ብሏል።

የአሁኑ ትውልድ የአባቶቹን የአንድነት እሴት መውረሱን በሕዳሴ ግድብ ግንባታ አስመስክሯል ያለው ኅብረቱ፤ የዘንድሮውን የኢሬቻ በዓል በዚሁ መንፈስ መላው ኢትዮጵያውያን በሰላም እና በአብሮነት እንዲያከብሩት ጥሪ አቅርቧል።

በአሊ ደደፎ

#EBCdotstream #Irreecha #HoraFinfine #HoraHarsadi