የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የወባ መከላከያ ክትባት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ደቡብ ኦሞ ዞን፣ ቱርሚ ከተማ ዛሬ አስጀምረዋል።
ክትባቱ ውጤታማነቱ በዓለም የጤና ድርጅት የተረጋገጠና አስተማማኝ መሆኑን ዶ/ር ደረጀ ዘመቻውን ባስጀመሩበት ወቅት ተናግረዋል።
ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ለሆነ ህፃናት በዘመቻ መልክ የሚሰጠው ክትባት የወባ ስርጭት ያለባቸው 58 ወረዳዎችን እንደሚያካልል ገልጸዋል።
በእነዚህ አካባቢዎት የሚኖሩ ወላጆችና አሳዳጊዎች ህፃናቱን በማስከተብ ግዴታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።
ከክትባቱ በተጨማሪ ከ3.5 ሚሊዮን በላይ የአልጋ አጎበሮች ለወባ ተጋላጭ ለሆኑ አካባቢዎች እንደሚሰራጩ ተገልጿል።
በተመስገን ተስፋዬ
#EBCdotstream #Ethiopia #Malaria #Vaccination