በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ''የባህል ልማታችን ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን'' በሚል መሪ ሃሳብ የሚከበረው 10ኛዉ ዙር የከምባታ ዞን ሕዝቦች የባህል ፣ ታሪክ ፣ ቋንቋ እና ልማት ሲምፖዚየም መካሄድ ጀምሯል።
ዛሬ በተጀመረው ሲምፖዚየም ላይ የከምባታ ዘመን መለወጫ በዓል የሆነው መሳላ እና አንድነት ላይ ያተኮሩ ጥናታዊ ፅሁፎች እንደሚቀርቡ ታውቋል።

የከምባታን ባህል ቋንቋ እና ታሪክ በማሳደግ ለትውልድ እንዲተላለፍ የተሰሩ ሥራዎችን መለስ ብሎ የሚቃኘው ይህ መድረክ፤ በጉዳዩ ላይ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያመላክታል ተብሎ ይጠበቃል።
በመድረኩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማሕበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፍቃዱን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የአካባቢው ተወላጅ ምሁራን እና የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በገነት ደንሰሞ እና ሲሳይ ደበበ