Search

የአተካና ምሽት በዱራሜ

ዓርብ መስከረም 09, 2018 156

በከምባታ የዘመን መለወጫ ‘‘መሳላ’’ በዓል ዋዜማ የሚከበረው የአተካና ስነ-ስርዓት በማህበረሰቡ ልዩ ቦታ የሚሰጠው የመሳላ በዓል ሌላኛው ድምቀት ነው፡፡

በአካባቢው ባህል መሰረት ከእርድ ቀን አስቀድሞ የሚከበረው የእናቶች መሳላ በመባል የሚታወቀው የአተካና እራት የመብላት ስነ-ስርዓት በዱራሜ ከተማ በኡቱቢያ ወጋ አደባባይ በድምቀት እየተካሄደ ይገኛል።

ይህ የአተካና ስነስርዓት የከምባታ እናቶች ለወራት ተጨንቀውና ተጠበው የሚያዘጋጁት የመሳላ በዓል አከባበር አንዱ አካል ነው።

የአዲስ ዓመት መግባትን ማብሰሪያ ተደርጎ የሚወሰደው ይህ ስነ-ስርዓት፤ በቤተሰብ አባላትና ዘመድ ጎረቤት በጉጉት የሚጠበቅ ነው።

ከአተካና እራት ስነ-ስርዓት ቁጥሎ በጉጉት የሚጠበቀው የመሳላ ወይም የከምባታ ዘመን መለወጫ በዓል በነገው ዕለት ይከበራል።

በሲሳይ ደበበ

#ebc #ebcdotstream #Ethiopia #Kembata #መሳላ