ከዋዜማው ጀምሮ በባህል፣ ቋንቋና ታሪክ ሲፖዚየም እንዲሁም በአተካና ባህላዊ የምግብ ምሽት በድምቀት በመከበር ላይ ያለው የከምባታ ዞን ህዝቦች ዘመን መለወጫ መሳላ በዓል ዛሬም በዱራሜ ስታዲየም በተለያዩ ባህላዊ ትዕይንቶች መከበሩን እንደቀጠለ ነው።
በክብረ-በዓሉ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አንተነህ ፍቃዱ እና የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ምሁራን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን፤ የህዝቡን ታሪክ እና አኗኗር የሚያሳየውን ኤግዚቢሽንም ጎብኝተዋል።
በሲሳይ ደበበ
#Ethiopia #Kembata #NewYear #Masala