Search

የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ስልጠና ሲወስዱ የቆዩ 300 አዳጊዎች ተመረቁ

ቅዳሜ መስከረም 10, 2018 133

የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የክረምት ስልጠና ሲሰጣቸው የቆዩ አዳጊዎችን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት አስመርቋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በንግግራቸው፥ ከዓለም የቴክኖሎጂ ዕድገት ጋር ተያይዞ ሊመጣብን የሚችለውን ጫና መቋቋም እንድንችል ዘመኑን የዋጁና ከአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አብዮት ጋር የሚናበቡ ታዳጊዎች ላይ መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል።

ይህ ትውልድ እኛ ያለፈን ዕድል ሊያልፈው፤ ግጭት፣ ጦርነት እና ችግር ሊወርስ አይገባውም ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለአዳጊዎች እየተሰጠ ያለው የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ስልጠና ቴክኖሎጂውን በመጠቀም ችግር ፈቺ የፈጠራ ሀሳቦችን እንዲያፈልቁ የሚያስችላቸው ስለመሆኑ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ትልቁን የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት መገንባቷን በማንሳትም የሀገሪቱን የዲጂታላይዜሽን ጉዞ የሚያፋጥኑ ዘርፈ ብዙ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አሳውቀዋል።

የተለያዩ ምዘናዎችን አልፈው ለምረቃ የበቁት አዳጊዎቹ በመደበኛ ትምህርቶቻቸው ላይም እንዲበረቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አደራ ብለዋል።

በአሸናፊ እንዳለ

#EBCdotstream #EthiopianAII #ArtificialIntelligence