የሕዳሴ ግድብ የተጠናቀቀው ተባብረው በሠሩ ክንዶች፤ በብስለት በተመሩ የዲፕሎማሲ ሥራዎች፤ በተደመረ የሀገር ሃብት እና ትውልዳዊ ኃላፊነት ነው ሲሉ የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
የታታሪ ሕዝቦች አምባ፣ የእንቁ ባህላዊ እሴቶች መገኛ፣ የበርበሬ አምራቾቹ እና የእንሰት ወዳጆቹ ምድር የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሕዳሴ መጠናቀቅ የልማት ሰንደቁን በድል አውለብልቧል ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ ዛሬ የተደረገው የድጋፍ ሰልፍ ክልሉ የእስከዛሬ ስኬቶችን እሴት በማድረግ ለታላላቅ ሀገራዊ የልማት ግቦቻችን ያለውን መሻት ያሳየ ነው ብለዋል።
ለኢትዮጵያ ልዕልና ከላብ እስከ ደም ጠብታ የመታገል እንዲሁም ሀገር በምትፈልገን በሁሉም የልማት ሰልፎች ፊት ቀድሞ የመገኘት የጋራ አቋምን ዛሬ በድጋፍ ሰልፉ አይተናል ነው ያሉት።
የሕዳሴን ድል መርህ እና አርዓያ ያደረገ ልማት ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በቀጣይ ይጠበቃል ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።
#EBCdotstream #Ethiopia #GERD #ሕዳሴግድብ