የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት ከአንድ ሺህ በላይ የአቪዬሽን ባለሞያዎችን በደማቅ ሥነ-ሥርዓት አስመረቋል።
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የአየር መንገዱ የቦርድ ሰብሳቢ ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ፣ ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ መስፍን ጣሰው እንዲሁም የአየር መንገዱ ከፍተኛ አመራሮች እና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።
ተመራቂዎቹ ከዩኒቨርሲቲው የፓይለት፣ የበረራ አስተናጋጅ፣ የአውሮፕላን ጥገና፣ የማርሻሊንግ እና ኤሮብሪጅ፣ እንዲሁም የንግድ እና የግራውንድ ሰርቪስ ትምህርት ቤቶች የተመረቁ መሆናቸውን አየር መንገዱ ለኢቢሲ በላከው መረጃ ገልጿል።
#EBCdotstream #Ethiopia #AviationUniversity #EthiopianAirlines #EAL