ዛሬ በወላይታ ሶዶ የተካሄደው ሲምፖዚየም ብሔሩ ያሉትን የባህል፣ የቋንቋና ሌሎች እሴቶች ለማሳደግ ትልቅ ድርሻ እንዳለው ተገልጿል።
የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሳሙኤል ተሰማ፥ የብሔሩ ቋንቋና ባህሉ ሳይበረዝ ለቀጣዩ ትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል።
በዚህም ከጊዜ ወደ ጊዜ ቋንቋውን ለማወቅና ባህሉንም ለመጠበቅ የሚጥር ትውልድ እየተፈጠረ እንደሆነ አንስተዋል።
የወላይታ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሀላፊ ምህረቱ ሳሙኤል በበኩላቸው፥ በተደረጉ ጥረቶች በዞኑ ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩ እንዲማሩ እና የዞኑ የሥራ ቋንቋ ወላይትኛ እንዲሆን ማድረግ መቻሉን አንስተዋል።
የወላይታ ብሄር የዘመን መለወጫ የ"ጊፋታ" በዓል በነገው ዕለት በድምቀት ይከበራል።
በአታላይ ፀሐይ
#EBCdotstream #Ethiopia #Wolaita #NewYear #Gifata