የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ "ጊፋታ" በዓል በወላይታ ሶዶ ከተማ በመከበር ላይ ይገኛል፡፡
የዘንድሮው የጊፋታ በዓል "ጊፋታ ለህብረ ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል ነው እየተከበረ የሚገኘው።
የጊፋታ በዓል በወላይታ ብሔር ዘንድ ከአሮጌው ዘመን ወደ አዲሱ ዘመን መሸጋገሪያና የአዲስ ዘመን ማብሰሪያ በዓል ነው፡፡
በዓሉ የአብሮነትና የአንድነት ዕሴቶችን ባቀፉ ስርዓቶችና ባህላዊ ኩነቶች እየተከበረ እንደሚገኝም ተመላክቷል፡፡
በበዓሉ ላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፣ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጂጌ (ዶ/ር) እንዲሁም ሌሎች የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
#ebc #ebcdotstream #Ethiopia #Wolaita #Gifata #festival