Search

ጎንደርን ታሪኳን የሚመጥን ገፅታ ለማላበስ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት

እሑድ መስከረም 11, 2018 50

የጎንደር ከተማ የኮሪደር ልማት የከተማዋን ገፅታ መለወጡን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ተናገሩ።

ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ከሌለች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ከጎንደር ከተማ አመራሮች ጋር በመሆን በከተማዋ እየተከናወኑ ያሉ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።

በጎንደር ከተማ አስተዳደር እየተከናወኑ የሚገኙት የኮሪደር ልማት ሥራዎች የከተማዋን ውበት በመጨመር የቱሪዝም ፍሰትን እንደሚያሳድጉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ገልጸዋል።

ጎንደር ታሪካዊ ከተማ ናት ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ታሪኳን የሚመጥን ገፅታ እንድትላበስ በከተማዋ የተጀመሩ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን አጠናክሮ መቀጠል ይገባል ብለዋል።

በከተማዋ በመንግሥትና በኅብረተሰብ ቅንጅት ከአፄ ቴዎድሮስ አየር ማረፊያ እስከ አፄ ቴዎድሮስ ሐውልት ያለውን የ15 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር መንገድ ያካለለ የኮሪደር ልማት ሥራ ማከናወን መቻሉን የጎንደር ከተማ አስተዳድር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው ተናግረዋል።

ከ2 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበት በቀን እና በሌሊት እየተከናወነ ባለው የኮሪደር ልማት 15 ሺህ ለሚጠጉ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉም ተገልጿል።

በራሔል ፍሬው

#EBCdotstream #Gondar #corridordevelopment