Search

በአዲስ አበባ እና በተወሰኑ የክልል ከተሞች በከፊል የኃይል መቋረጥ ተከስቷል

እሑድ መስከረም 11, 2018 47

በአዲስ አበባ እና በተወሰኑ የክልል ከተሞች በከፊል የኃይል መቋረጥ መከሰቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።

ከሰበታ ቁጥር 1 የኃይል ማከፋፊያ ጣቢያ ወደ ጥቁር አንበሳ ኃይል ማከፋፊያ ጣቢያ፤ ከጥቁር አንበሳ ኃይል ማከፋፊያ ጣቢያ ወደ አዲስ ዌስት ወይም ኮልፌ ማከፋፈያ ጣቢያ በተዘረጋው 132 .ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ መደበኛ የጥገና ሥራ ሲከናወን መዋሉን ተቋሙ ገልጿል።

ይሁንና ጥገናው ተጠናቆ መስመር በሚሞከርበት ጊዜ በተፈጠረ የመስመሮች መነካካት በአዲስ አበባ እና በተወሰኑ የክልል ከተሞች የኃይል አቅርቦት መቋረጡን ነው ያስታወቀው።  

የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ርብርብ እየተደረገ በመሆኑ፤ መስመር በተቋረጠባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ደንበኞቹ በትዕግስት እንዲጠብቁ ጠይቋል።

#EBCdotstream #EEP #power