የሐረሪ ክልል ነዋሪዎች ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክተው የድጋፍ ሰልፍ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።
የድጋፍ ሰልፉ "በህብረት ችለናል" በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ ይገኛል።

የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና በገጠርና ከተማ ወረዳዎች የሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በድጋፍ ሰልፉ እየተሳተፉ ናቸው።
በድጋፍ ሰልፉ ላይ
"የሕዳሴው ግድብ የኢትዮጵያ ማንሰራራት ምልክት!"
"የሕዳሴው ግድብ የብልፅግናችን አሻራ!"
"ግድባችን የመቻል ማሳያ የማንሰራራት ጅማሮ ምልክት!"
"ግድባችን በራሳችን አቅም የገነባነው የአንድነታችንና የአብሮነታችን ምሰሶ!"
የሚሉና ሌሎች መልዕክቶችን የያዙ መፈክሮች በመሰማት ላይ ይገኛሉ።