በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አማኞች ዘንድ በመጪው ዓርብ የሚከበረውን የመስቀል ደመራ በዓል በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ለማክበር ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ቤተ-ክርስቲያኒቱ አስታውቃለች።
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ-ክህነት ሥራ አስኪያጅና የመስቀል በዓል አዘጋጅ ዐቢይ ኮሚቴ ሰብሳቢ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ መስከረም 16 ቀን 2018ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የሚከበረው በዓል በሰላም እና በስኬት እንዲጠናቀቅ ከተለያዩ ተቋማትና የፀጥታ አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
በዓሉ የኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምና ፍቅርን የሚገለፅበት መሆኑን የገለፁት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ፤ ሁሉም ምዕመን በበዓሉ ወቅት ከአለባበስ ጀሞሮ ክርስቲያናዊ ሥርዓትን እንዲከተል አሳስበዋል።
በዓሉ ዓለም አቀፋዊ በዓል መሆኑንም ገልጸው፤ ሁሉም ምዕመን በዓሉ በስኬት እንዲጠናቀቅ የበኩሉን ኃላፊነትና ትብብር እንዲያጠናክርም ጠይቀዋል።
በይድነቃቸው ሰማው