Search

በክልሉ ሰላምና ፀጥታ ለማስፈን የሚሰራው ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል፦ ርዕሰ መሥተዳድር አሻድሊ ሀሰን

ሰኞ መስከረም 12, 2018 33

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፀጥታ ዘርፉን ማጠናከር ያለመ የውይይት መድረክ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በተገኙበት በአሶሳ ከተማ ተካሂዷል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት፣ የፀጥታ ኃይሎች ራሳቸውን መሥዕዋት በማድረግ ሕዝቡ በሰላም እና ልማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለሚከፍሉት ዋጋ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።
የሕዝቡን የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ለመመለስ የአካባቢውን ዘላቂ ሠላም እና ፀጥታ ማስከበር ቀዳሚው ተግባር እንደሆነም አንስተዋል።
ባለፈው በጀት ዓመት በክልሉ ሰላምን ለማስፈን የተሰሩ አበረታች ሥራዎችን በቀጣይም አጠናክሮ ለማስቀጠል የሁሉም ርብርብ እንደሚያስፈልግ ርዕሰ መስተዳደሩ ገልጸዋል።
የክልሉ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ቢኒያም መንገሻ በበኩላቸው፤ መጪው ሀገራዊ ምርጫ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከናወን ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
በውይይት መድረኩ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና የክልሉ ፀጥታ ኃይል አመራሮች ተገኝተዋል።
በነስረዲን ሀሚድ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ተያያዥ ዜናዎች: