የዛሬ አምስት ዓመት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 75ኛ ጉባዔ ላይ ቻይና በአባል ሀገራቱ የተነሳባትን የታዳሽ ኃይል አጠቃቀም ችግር ለመፍታት ቃል የገባችበት ጊዜ ነበር።
በቻይና የሚገኙ አብዛኞቹ ኢንዱስትሪዎች የሚጠቀሙት ኃይል ለአካባቢ ብክለት ከፍተኛ ሚና የነበራቸውም ነበሩ።
ቻይና በፖሊሲዋ ላይ ባደረገችው ለውጥ በካይ ያልሆኑ ንፁህ ኢነርጂ የሚገኝባቸውን ዘርፎች በመለየት፣ የኤሌክትሪክ ኃይልን ከውኃ፣ ኒውክሌር፣ ከንፋስ እና ፀሐይ በማግኘት ሰፊ ሥራን ሰርታለች።
የሰራችው ስራ ለውጥ አምጥቶ በ2024 ብቻ 3.71 ትሪሊዮን ኪሎ ዋት ኢነርጂን ታዳሽ ከሆኑ የኃይል አማራጮች በማምረት፣ ለዘርፉ የሰጠችውን ልዩ ትኩረት እና የገባችውን ቃል መፈጸሟን በተግባር እያሳየች ትገኛለች፡፡
በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን በኤሌክትሪክ በሚሰሩ የመተካት እና ከሀገር ውስጥ አልፎ በዓለም ገበያዎች ላይ ተፅዕኖ መፍጠር ላይ ትኩረት አድርጋ በመስራቷ፣ ዛሬ ላይ በኤሌክትሪክ መኪኖች የዓለም አቀፍ ገበያን እየተቆጣጠረች ትገኛለች፡፡
ቻይና ከ2016 ጀምሮ ከ 24.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ በአየር ንብረት ለውጥ ለተጎዱ ታዳጊ ሀገራት በእርዳታ መልክ መስጠቷንም ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
በሀብተሚካኤል ክፍሉ