የሕዳሴ ግድብ ከጫፍ እስከ ጫፍ በሁሉም የኢትዮጵያ ማዕዘናት የኢትዮጵያ ልጆችን ለልማት ያስተባበረ፣ የመደመር ዕሳቤ የታተመበት ፕሮጀክት ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ተራሮች በሸለቆ እና በሜዳ ገሰግሶ እንደሚገናኘው፣ ታላቁ ዓባይ የብዝኅነት ቤት በሆነችው ድሬዳዋ የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን ተከትሎ ዛሬ የድጋፍ ሰልፍ ተደርጓል ብለዋል፡፡
በሕዳሴ ግድብ ያየናቸው በፈተናዎች መካከል እንደ አለት ጸንቶ በመቆም ማሸነፍ በደሬዳዋ ያሉ የልማት አቅሞችን ለሀገር ልማት ለማዋል ብርታት ይፈጥራል ብለዋል፡፡
ድሬዳዋ የሰላም እና የፍቅር ብቻ ሳይሆን ልማት እና ለለውጥ መበርታትም መገለጫዋ ነው ሲሉም ገልጸዋል ።