Search

የአፍሪካ ምርጥ የአገልግሎት ማዕከል ተብሎ የተመረጠው መሶብ

ሰኞ መስከረም 12, 2018 39

መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የአፍሪካ የአንድ ማዕከል የሕዝብ አገልግሎት አቅራቢ ሞዴል ሆኖ መመረጡን የአገልግሎቱ ኮሙዩኒኬሽን ዲፓርትመንት አስተባባሪ ስብሃት ግርማ በተለይ ለኢቢሲ ዶት ስትሪም ገልጸዋል።
በቻይና በሚገኘው ‘ኦል ኢንተለጀንስ ኒው አፍሪካ ሁዋዌ ኮኔክሽን 2025’ በተዘጋጀው መድረክ ላይ ማዕከሉ ሥራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ያከናወናቸውን ዋና ዋና ተግባራት የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር አንተነህ ማሞ ዘርዝረዋል።
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሥራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ውጤታማ ሥራዎችን እየሠራ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ጠቅሰዋል፡፡
ማዕከሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ የደረሰበት ውጤታማ ምዕራፍ የመሶብ ቤተሰብ ቁርጠኝነት ማሳያ መሆኑንም ነው ያነሱት፡፡
ስኬቱ የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ እና ፈጠራን እና ቴክኖሎጂን በማከል የሕዝብ አገልግሎትን የላቀ ደረጃ ላይ ማድረስ እንደሚቻልም ተቋሙ ገልጿል፡፡
ዕውቅናው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ያሳየው አስደናቂ ጅማሮ አዳዲስ ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን የማውጣት እና የመተግበር አቅም ማሳያ ምልክት እንደሆነም ነው የተጠቀሰው።
ይህ ጅምር ብቻ መሆኑን የጠቀሰው ማዕከሉ፤ ከኢትዮጵያም አልፎ በአፍሪካ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ አርዓያ የሆነ ቀልጣፋ እና በቴክኖሎጂ የታገዘ ዜጎችን ያማከለ አገልግሎትን የላቀ ደረጃ ላይ ለማድረስ እንሚሠራ አስታውቋል፡፡
በለሚ ታደሰ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ተያያዥ ዜናዎች: