ሕዳሴ በትውልዶች ሁሉ በታላቅ የቃል ግርማ የሚነገር፣ ይህ ትውልድ በላብ በደም እና በሃሳብ ታግሎ ያሸነፈው አንጸባራቂ ድል ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው፤ የቀደመ የስልጣኔ ቀለም እና ዐሻራ ዛሬ ድረስ ያደመቃት ሐረር የዚህ ትውልድ አሻራ በሆነው የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ የልማት ድል ሰልፍ አድርጋለች ብለዋል።
በሕዳሴ ግድብ የታየው የመቻል ምልክት፣ የትብብር ውጤትና የአብሮነት ጉልበት እንደ ሐረር ላሉ በሰላም እና ተከባብሮ መኖርን መሰረት ላደረጉ ክልሎች ትልቅ ዕሴትን ይጨምራልም ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ሐረር የዚህ የልማት ድል ነጋሪ ብቻ ሳይሆን ተጋሪ መሆኗን በጀመረቻቸው ልማቶች እያሳየች ትገኛለች ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡