Search

በፕሬዝዳንት ታየ አፅቀሥላሴ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ በ80ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ እየተሳተፈ ነው

ሰኞ መስከረም 12, 2018 54

በፕሬዝዳንት ታየ አፅቀሥላሴ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በ80ኛው የተባበሩት መንግስሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ተሳትፎ ለማድረግ ኒውዮርክ ገብቷል። 

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሃደራ አበራን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት ያካተተው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በኒውዮርክ ''ደህናነት በአብሮነት'' በሚል መሪ ሀሳብ በሚካሄደው የተመድ 80ኛ ጠቅላላ ጉባዔ ተሳትፎውን ጀምሯል።

ኢትዮጵያ በጉባዔው ላይ የራሷን  ብሔራዊ ጥቅሞች እና የአፍሪካን ጥቅሞች በሚያስጠብቁ ጉዳዮች ላይ ንቁና ጠንካራ ተሳትፎ እንደምታደርግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ከዋናው ጉባዔ ተሳትፎ በተጨማሪ በርካታ የሁለትዮሽና የባለብዙ ወገን የጎንዮሽ የውይይት መድረኮች ላይም ኢትዮጵያ የራሷን ብሄራዊ ጥቅሞች ቅድሚያ ሰጥታ ተሳትፎ እንደምታደርግ ተመላክቷል።

ዓለማችን በተለያዩ ሠላምና ፀጥታ ጉዳዮች እየተፈተነች ባለበት ወቅት የሚከበረው የተመድ 80ኛ ዓመት አባል ሀገራት ከመቼውም ጊዜ በላይ አብሮነታቸውን በማጠናከር የተሻለች ዓለም ለመፍጠር መሥራት እንደሚገባቸው ተገልጿል።

#ebc #ebcdotstream #Ethiopia #MFA #UNGA_80

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ተያያዥ ዜናዎች: