የመደመር መንግሥት በተለየ መልኩ ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ ሞዴል ሆኖ የመጣ መሆኑን የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
"የመደመር ወግ" በሚል ርዕስ የመደመር መንግስት መጽሐፍን አስመልክቶ በተካሄደው ውይይት ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)፤ የፖለቲካ፣ የማህበራዊና የኢኮኖሚ ስርዓታችን በገንዘብ ተጠልፎ ፖለቲካችንን ሀሳብ አልባ አድርጎት ቆይቷል ብለዋል፡፡
በአንድ ሀገር ውስጥ የፖለቲካ ገበያ ሲኖር ተቋም በስርዓት እንደሚገነባ፤ የተገነባ ስርዓትና ተቋም አሰራር ስለሚያበጅ ስልጣን ወደ ተገቢው አካል እንዲሄድ እንደሚያስችል መፅሐፉ እንደሚዘረዝር ሚኒስትሯ ገልፀዋል፡፡
ስልጣን ለህዝብ ጥቅም ሳይሆን ለግል ጥቅም የማዋል ታሪክ ውስጥ መክረማችን የፖለቲካ ስርዓታችን ሀሳብ አልባ እንዲሆን አድርጎት እንደቆየም በመፅሐፉ መገለፁን ነው የተናገሩት፡፡
የመደመር መንግሥት እሳቤው አዲስ ያልተሄደበትን መንገድ መርጠናል፣ በዛ ለመጓዝ ነው ይሄንን ያሰብነው ሲል ይጠቁማል ብለዋል፡፡
መፅሐፉ እንደ ሀገር ትክክለኛውን መልስ ከመፈለግ በፊት ትክክለኛውን ጥያቄ ማንሳት እንደሚቀድም በዝርዝር ያስቀምጣል ነው ያሉት፡፡
መፅሐፉ የማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ስርዓታችን፤ ለስራ ያለን አመለካከት ከሀሳብና ከባህል አኳያ አለመለወጡን በቁጭት እንደሚያነሳ የገለፁት ሚኒስትሯ፤ ለሀገር የተሻለን ነገር ለመፍጠር እነዚህ ጉዳዮች መለወጥ እንዳባቸው የመደመር መንግስት መፅሐፍ ይጠይቃል ብለዋል፡፡
በላሉ ኢታላ
#EBC #ebcdotstream #AbiyAhmedAli #መደመር #YemedemerMengist