በሴራሊዮን ከተጠራው 80ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ማሻሻያ የአስር መሪዎች ኮሚቴ 7ኛ ጉባዔውን አድርጓል።
የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በጉባዔው ባሰሙት ንግግር፥ አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ተገቢ ውክልና እንዲኖራት የሕብረቱ አባል ሀገራት ሁሉንም አማራጮች በመጠቀም በጋራ ድምፃቸውን እንዲያሰሙ ጥሪ አቅርበዋል።
ፕሬዚዳንት ሩቶ በንግግራቸው፥ ከዓለም ህዝብ ውስጥ 20 በመቶ ገደማውን የያዘችው አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ተገቢውን ውክልና አለማግኘቷ በምንም ሁኔታ ተቀባይነት የለውም ብለዋል።
ተመድ ለተቋቋመበት ዓላማ ብቁ ይሆን ዘንድ በፀጥታው ምክር ቤት ያለውን ኢ-ፍትሐዊ አሠራር ማስተካከል እንደሚገባ አፅንፆት ሰጥተዋል።
የአፍሪካ ሀገራትም በተቋሙ ፍትሐዊ ውክልና እንዲኖራቸው ተቀናጅተው በመሥራት ግፊት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴን ጨምሮ የሀገራት መሪዎች እየተሳተፉበት ያለው 80ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ከትናንት ጀምሮ እየተካሄደ ይገኛል።
በላሉ ኢታላ
#EBCdotstream #UNGA #UNSC #Reform #CommitteeofTen