Search

ትውልዱ የባሕር በር ጥያቄን እንደ ብሔራዊ መዝሙሩ ማድረግ አለበት

ማክሰኞ መስከረም 13, 2018 215

ትውልዱ የባሕር በር ጥያቄን እንደ ብሔራዊ መዝሙሩ አድርጎ መዘመር አለበት ሲሉ የታሪክ መምህር እና ተመራማሪው በለጠ ሲጌቦ ገለጹ።

መምህር በለጠ ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ፥ ኢትዮጵያ በራሷ አቅም፣ በህዝቧ ርብርብ የሕዳሴ ግድብን እውን አድርጋለች ብለዋል።

በቀጣይ ደግሞ ሙሉ ትኩረቷን ብሔራዊ እሳቤ እና የሕልውና ጉዳይ በሆነው የባሕር በር ላይ ታደርጋለች ሲሉ ገልጸዋል።

ለህዝቡ የታሪክ ቁጭት ምላሽ ለመስጠት ኢትዮጵያ የባሕር በር ማግኘት አለባት ያሉት ተመራማሪው፤ ይህን መብቷን ለማስከበር ሀገሪቱ ዲፕሎማሲያዊ፣ ሕጋዊ እና ሰላማዊ መንገድ እንደምትከተል አክለዋል።

ክርስትናም ሆነ እስልምና ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ በባሕር መግባታቸውን አንስተው፤ የሀገሪቱ የስልጣኔ ምንጭ የባህር በር እንደነበር ተናግረዋል።

ኢትዮጵያን ከባሕር በር ለማሸሽ ሆን ተብሎ መሠራቱን ጠቅሰው፤ ከታሪካዊው ጥፋት በመማር አሁን መንግሥት እና ሕዝብ ለባሕር በር ጥያቄ ከፍተኛ ትኩረት መስጠታቸው  ይበል የሚያሰኝ ስለመሆኑም ነው ያነሱት።

በሜሮን ንብረት

#EBCdotstream #Ethiopia #port #seaport