Search

ለኢኮ ̵ ቱሪዝሙ ተደማሪ አቅምን የፈጠረው ሕዳሴ

ማክሰኞ መስከረም 13, 2018 769

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከኃይል ማመንጫነት ባለፈ ለኢኮ-ቱሪዝም እና ለመዝናኛነት የሚውል ዕምቅ አቅም እንዳለው የተለያዩ ምሁራን ሲገልጹ ይደመጣል።
በተለይ በግድቡ አማካኝነት የተፈጠረው ንጋት ሐይቅ ለአካባቢው ውበትን ከማላበስ ባለፈ የቱሪዝም ገቢን ለማሳደግ ወሳኝ ድርሻ እንደሚኖረው ይጠበቃል።
የታሪክ እና የፖለቲካ ሳይንስ ጉዳዮች ተንታኝ የሆኑት አለማየሁ አረዳ (ዶ/ር) ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ግድቡ የኢኮ ̵ ቱሪዝምን በማስፋፋት ተደማሪ የኢኮኖሚ ገቢን ለመፍጠር ወሳኝ ሚና እንዳለው አስረድተዋል።
በሕዳሴ ግድብ አማካኝነት የሚገኘው የቱሪስት ፍሰት ለጎረቤት ሀገራትም ጭምር የሚተርፍ ትሩፋት እንደሚኖረውም ነው የገለጹት፡፡
የሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ፍቅርተ ታምር በበኩላቸው፤ ግድቡ የውጭ ምንዛሬን እና የእውቀት አድማስን የሚያሰፋ ነው ብለዋል፡፡
በዓባይ ወንዝ ተፋሰስ ላይ የተተከሉ ችግኞችም የአካባቢውን ምህዳር እንደለወጡት አንስተው፤ ሕዳሴ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች ያሉት ፕሮጀክት መሆኑንም ገልጸዋል።
 
በሜሮን ንብረት