ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በራስ አቅም መገንባቱ የብዝሃነት እና የመደመር ማዕቀፍ ነፀብራቅ ነው ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የውኃ ሀብት ምህንድስና መምህሩ በለጠ ብርሃኑ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
የግድቡ ግንባታ በራስ አቅም ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ከማሳካት ባሻገር በሕብረ ብሔራዊ አንድነት የላቀ ውጤት ማምጣት እንደሚቻል ትምህርት የሰጠ ነው ብለዋል።

ሕዳሴ እችላለሁ የሚለውን ስሜት በእያንዳንዱ ዜጋ ላይ እንዲሰርጽ ያደረገ ግዙፍ ፕሮጀክት መሆኑንም ተናግረዋል።
ሕዳሴ ኢትዮጵያ የማንንም ድጋፍ ባታገኝም የእራሷ እሳቤ ያላት እና ሉዓላዊነቷን ያስከበረች ሀገር መሆኗን በተግባር ያረጋገጠ ውጤታማ ፕሮጀክት ነው ሲሉም ገልጸዋል።