ከ80ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሃደራ አበራ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ከፍተኛ ባለሥልጣን አምባሳደር ጆናታን ጂ. ፕራት ጋር በጋራ ፍላጎቶች ዙሪያ ተወያይተዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ያለውን ጠንካራ ግንኙነት በማድነቅ በጋራ ፍላጎቶች ዙሪያ ቀጣይነት ያለው ውይይት የማካሄድ አስፈላጊነትን ገልጸዋል።
አምባሳደር ሃደራ ለአምባሳደር ፕራት በወቅታዊ የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ዙሪያ ገለጻ አድርገውላቸዋል።
አምባሳደር ፕራት በበኩላቸው አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ሽብርተኝነትን በጋራ በመዋጋት፣ በቀጣናው ሰላም እና ደኀንነት ዙሪያ በትብብር መሥራት እንደምትቀጥል ያላትን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።
ሁለቱ ወገኖች በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የንግድ ግንኙነት ማሻሻል የሚያስችሉ ሥራዎችን ለማከናወን መስማማታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
#EBCdotstream #UNGA #Ethiopia #USA #bilateral