Search

ኢትዮጵያ ያነሳቸው የባሕር በር ጥያቄ ዓለም ዓቀፍ መርሆዎችን የተከተለ ተገቢ የመብት ጥያቄ ነው

ረቡዕ መስከረም 14, 2018 36

ኢትዮጵያ ውስጥ የተለያየ የፖለቲካ አመለካከት ያላቸው አካላት ቢኖሩም በሀገሪቱ የባሕር በር ጥያቄ ላይ ግን  በጋራ መቆም ይገባቸዋል ሲሉ የሕግ መምህርና ተመራማሪው ማናዬ ዘገየ (ዶ/ር) ገለጹ።

ዶ/ር ማናዬ ከኢቲቪ ዳጉ መሰናዶ ጋር በነበራቸው ቆይታ፥ ኢትዮጵያውያን የፖለቲካ ልዩነታቸውን ወደ ጎን በመተው የሀገር ሕልውና መሠረት በሆነው የባሕር በር ጥያቄ ላይ በጋራ መቆም ይኖርባቸዋል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ያነሳቸው  የባሕር በር ጥያቄ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን የተከተለ ተገቢ የመብት ጥያቄ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል ሲሉ  ገልጸዋል።

ዓለም አቀፍ ሕግ እና ተሞክሮ እንደሚያሳየው፥ አንድ ሀገር ምርቶችን  ወደ ዓለም ገበያ ለማውጣት ወይም ከዓለም ገበያ ለማስገባት የጎረቤት አገራትን የባሕር በር መጠቀም ይፈቀድለታል።

ኢትዮጵያ የባሕር በር አግኝታ በንግድና ኢኮኖሚ ተጠቃሚ ብትሆን ለጎረቤት አገራት ምንም ዓይነት ጉዳት እንደሌለው ዶ/ር ማናዬ አንስተዋል።

በስምምነት ወደብ ካለሙ ሀገራት መካከል ዛምቢያ፣ ስዊዘርላንድ እና አፍጋኒስታንን በአብነት ጠቅሰው፤ ኢትዮጵያም ከእነርሱ ተሞክሮ በመውሰድ በስምምነት የባሕር በር ማግኘት ይገባታል ብለዋል።

የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት በዓለም አቀፍ ደረጃ 44 ሲሆኑ፤ ከእነዚህ ውስጥ 16ቱ አፍሪካ ውስጥ ይገኛሉ።

በቢታንያ ሲሳይ

#EBCdotstream #Ethiopia #seaport