Search

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ለአዲሱ የማላዊ ፕሬዚዳንት የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት አስተላለፈ

ሓሙስ መስከረም 15, 2018 75

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማሕሙድ ዓሊ ዩሱፍ ለአዲሱ የማላዊ ፕሬዚዳንት አርተር ፒተር ሙታሪካ የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት አስተላልፈዋል። ማላዊያን ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እንዲሁም በሕዝቡ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ምርጫ በማድረጋችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል የኅብረቱ ሊቀመንበር። ማሕሙድ ዓሊ ዩሱፍ በምርጫው ተሳትፈው ሽንፈታቸውን በፀጋ ለተቀበሉት ለቀድሞው የማላዊ ፕሬዚዳንት ላዛሩስ ቻክዌራም አድናቆታቸውን ገልጸዋል። የአፍሪካ ኅብረት እና የኮሜሳ የጋራ የማላዊ ምርጫ ታዛቢ ቡድን ሊቀመንበር በመሆን ኃላፊነታቸውን በብቃት ለተወጡት ለቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያ ደሳለኝም ኮሚሽኑ ምስጋና አቅርቧል። በደጋፊዎቻቸው “አባታችን” በሚል ስም የሚጠሩት የ85 ዓመቱ አዲሱ የማላዊ ፕሬዚዳንት አርተር ፒተር ሙታሪካ የዴሞክራሲያዊ ፕሮግሬሲቭ ፓርቲን በመወክል የ3 ሚሊዮን መራጮችን ድምፅ በማግኘት ማሸነፍ መቻለቸውን ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ሙታሪካ ራሳቸውን ከፖለቲካ ካገለሉበት ወደ ምርጫ ተመልሰው ነው ማሸነፍ የቻሉት። በላሉ ኢታላ #ebcdotstream #Malawi #Malawielection #election #AU #Mutharika