Search

ኢትዮጵያ ለሶማሊያ ሰላም እና መረጋጋት የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ያላትን ቁርጠኝነት ገለጸች

ሓሙስ መስከረም 15, 2018 106

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሃደራ አበራ ከ80ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን በተካሄደው የሶማሊያ የአፍሪካ ኅብረት የድጋፍ እና ማረጋጊያ ተልዕኮ (AUSSOM) የከፍተኛ ደረጃ ኮንፈረንስ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ኢትዮጵያ ለሶማሊያ ሰላም እና መረጋጋት ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

አምባሳደር ሃደራ በሰጡት አስተያየት “የአልሸባብን አቅም በከፍተኛ ደረጃ በማዳካም ውጤት መገኘቱን አንሥተዋል። በዚህ ረገድ ለወታደሮቻችን በተለይም በሥራ ላይ እያሉ ሕይወታቸውን ላጡ ዋጋ ክብር እና ዋጋ እንሰጣለን ብለዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው ቡድኑ አሁንም ዓለም አቀፍ ስጋት የደቀነ በመሆኑ የተቀናጀ ዓለም አቀፍ እርምጃ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

የሶማሊያ መንግሥት የብሔራዊ መከላከያ እና የፀጥታ ኃይሎችን አቅም በማጠናከር ረገድ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴም አድንቀዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው AUSSOM ወሳኝ የፋይናንስ እጥረት እንዳለበት በመግለጽ አጋሮች ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩ እና ከአሁን በፊት የተላለፈው የተመድ ውሳኔ ገቢር እንዲሆን ጠይቀዋል።

የሶማሊያን የብሔራዊ ደኅንነት አቅም መገንባት ዘላቂ የመረጋጋት መንገድ መሆኑን  ሚኒስትር ዴኤታው አስምረውበታል።

ሶማሊያ ደኅንነቷ የተጠበቀ እና የበለጸገች ሀገር ሆና እንድትወጣ የታደሰ የፖለቲካ ቁርጠኝነት እና የተቀናጀ ድጋፍ እንዲደረግ መጠየቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

#MFA #AUSSOM #Ethiopia #Somalia