ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ጋር በሁለትዮሽና አለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፤ ከአለም አቀፍ የአቶሚክ ፎረም ጎን ለጎን ከቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ጋር በሁለትዮሽና አለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገናል ብለዋል።
የግብርና ሜካናይዜሽንን ጨምሮ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ጉዳዮች ላይ በጋራ በሚሰራበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።