Search

ከሩስያ ጋር የጋራ የኒኩሊየር ኃይል ማመንጫ ለማልማት ስምምነት ተፈራርመናል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ዓርብ መስከረም 16, 2018 136

ከፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በተለያዩ ዘርፎች ላይ አጠቃላይ ውይይት ማካሄዳቸውን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ እነዚህም የኃይል ማመንጫ፣ ግብርና፣ የጤና ዘርፍ ልማት እና የመከላከያ ትብብርን እንደሚያካትቱ ገልጸዋል።

በተለይም ለማኅበረሰብ አገልግሎት የሚውል ንፁህ ኃይል ለማቅረብ የጋራ የኒኩሊየር ኃይል ማመንጫ ለማልማት ስምምነቶችን በመፈራረም የጋራ ፍላጎቶቻችንን የሚያጎለብቱ ጉዳዮች ላይ ተማክረናል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሑፍ።

#EBCdotstream #Ethiopia #Russia #Agreement #AbiyAhmedAli #VladimirPutin