Search

በሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ የሚመክር መድረክ በባሕርዳር ተካሄደ

ዓርብ መስከረም 16, 2018 67

በባሕርዳር ከተማ በወቅታዊ የሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ የሚመክር መድረክ ተካሂዷል።
በመድረኩ በአማራ ክልል በአዊ፣ በደቡብ ጎንደር እና በጎጃም ክላስተር ያለው የሰላም እና ጸጥታ ሁኔታ በርካታ ለውጦች የታዩበት እንደሆነ ተነስቷል።
ሰላምን ዘላቂ እና አስተማማኝ ለማድረግ በቀጣይ የሚከናወኑ ቁልፍ ሥራዎች ላይ መግባባት መደረሱም ተመላክቷል።
በቀጣይ የክልሉን ሰላም አስተማማኝ በማድረግ ማኅበረሰቡ በሰላም ወጥቶ እንዲገባ እና በሙሉ አቅሙ ወደ ልማት ሥራዎች እንዲዞር ሰላሙን አስተማማኝ ማድረግ እንደሚገባም ተጠቁሟል።
በውይይት መድረኩ፤ የጦር ኃይሎች ምክትል ኢታማዦር ሹም ጀኔራል አበባው ታደሰ፣ የምሥራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል መሀመድ ተሰማ፣ የአማራ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ እሸቱ የሱፍ (ዶ/ር)፣ በምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር)፣ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዘላለም መንግሥቴ (ዶ/ር) እንዲሁም ሌሎች የክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ጄኔራል መኮንኖች፣ የዞን አሥተዳዳሪዎች እና ከንቲባዎች እንዲሁም በየደረጃው የሚገኙ የሥራ መሪዎች ተሳትፈዋል።
በራሔል ፍሬው