Search

ደመራ በድምቀት እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር ላደረጉ ምስጋና ይገባል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ዓርብ መስከረም 16, 2018 33

የዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል በርካታ ሕዝብ እና ቱሪስቶች በተገኙበት እጅግ በአማረ እና በደመቀ መልኩ በመስቀል አደባባይ መከበሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ።
በዓሉ በድምቀት፣ እሴቱን ጠብቆ እና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ላደረጋችሁ አካላት ሁሉ ምስጋና ይገባችኋል ሲሉም አስታውቀዋል።