የሕዳሴ ግድብ ለሀገራችን ዳግም ልደትን ያበሰረ ስኬት ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ገለፁ፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ለመስቀል በዓል ባስተላለፉት መልዕክት፣ የመስቀሉ ቃል ማለት ይቅርታን እና ዕርቅን፣ እኩልነትን እና አንድነትን እንዲሁም ፍትሕን ማረጋገጥ መሆኑን መገንዘብ ይገባል ብለዋል።
የዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል እግዚአብሔር የሰጠንን ውኃ በመጠቀም በአንድነት ተረባርበን የሕዳሴ ግድብን አጠናቀን ባስመረቅንበት ማግስት መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ የተጀመሩ ታላላቅና ዘመን ተሻጋሪ ሥራዎች እውን ማድረግ የሚቻለው ህዝቡ በአንድነትና በሕብረት ሲነሳ እንደሆነ ከህዳሴ ግድብ ተምረናል ሲሉም ገልፀዋል፡፡
የሕዳሴ ግድብ ለሀገራችን ዳግም ልደትን ያበሰረ ስኬት ነው ያሉት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፤ ለዚህ ላበቃን እግዚአብሔር እና በስራው ታሪካዊ አሻራቸውን ላስቀመጡ ሁሉ ምስጋና እናቀርባለን ብለዋል፡፡
በቀጣይ ለመስራት በዕቅድ የተያዙ ታላላቅ የልማት ስራዎችን በጥራትና በፍጥነት ተሰርተው ለህዝብ ጥቅም እንዲውሉ መረባረብ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡
በአዲሱ ዓመት እርስ በርሳችን ከመጠፋፋት ይልቅ በጋራ ሠርተን በጋራ የምንለማበት ጉዳዮችን ምርጫችን እናድርግ ሲሉም አባታዊ ምክራቸውን አስተላልፈዋል።
#ebcdotstream #Ethiopia #Meskel #Demera