ቅርስ አንድን ሀገር በየዘመናቱ ያለፈችባቸውን ስልጣኔ፣ ባሕል፣ ወግ፣ ታሪክ፣ እሴት እና ማንነት ማሳያ ወይም መገለጫ ነው፡፡
ኢትዮጵያም በዚሁ ረገድ በዓለም ቅርስነት የተመዘገቡ በርካታ የቅርስ ሀብቶች ያሏት ሀገር ናት፡፡
በኢትዮጵያ የመስቀል በዓልን ጨምሮ የዓለም ሕዝብ በጉጉት የሚጎበኛቸው ልዩ እና ድንቅ የሆኑ ባህላዊና ተፈጥሮኣዊ ቅርሶች ይገኛሉ፡፡
ዩኔስኮ የመዘገባቸው ከ15 በላይ ቅርሶች ባለቤት የሆነችው ኢትዮጵያ፤ ቅርሶቿን በማስመዝገብ ከአፍሪካ በቀዳሚነት ተቀምጣለች፡፡
እንደ እ.አ.አ 1972 የአለም የዩኔስኮ ስምምነት (ዩኔስኮ ኮንቬንሽን) ከፀደቀ ጀምሮ ኢትዮጵያ በርካታ የሚዳሰሱ እና የማይዳሰሱ ቅርሶችን አስመዝግባለች፡፡
ኢትዮጵያ በዚህ ረገድ በተለያዩ የቅርስ ሀብቶች የታደለች ከመሆኗ ባሻገር በርካታ የቱሪስት መሰህቦችን በዓለም ደረጃ ለማስመዝገብ ችላለች።
በዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት ከተመዘገቡ ቅርሶች መካከልም የአክሱም ሐውልት፣ የላሊበላ ውቅር አብተ ክርስቲያናት፣ የመስቀል በዓል፣ የሰሜን ተራች ብሔራዊ ፓርክ፣ የጎንደር ቤተ-መንግስት፣ የጢያ ትክል ድንጋዮች፣ የታችኛው አዋሽ ሸለቆ፣ የሐረር ጀጎል ግንብ፣ የገዳ ሥርዓት እና ፍቼ ጫምባላላ ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡
የቱሪዝም ፀጋ ባለቤት የሆነችው ኢትዮጵያ መሰል የቅርስ ሐብቶችን ለቱሪዝም መዳረሻነት በማዋል ከዘርፉ ተገቢውን ጥቅም ማግኘት እንድትችል መሰረተ ልማቶችን ማሟላት ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡
ከጊዜ ወደ ጊዜ የቱሪዝም ዘርፉ ትኩረት እየተሰጠው የመጣ ሲሆን አዳዲስ የመዳረሻ ስፍራዎችን በማስፋፋት፣ ጥገና የሚያስፈልጋቸውን እድሳት በማድረግ እና በመጠበቅ ትኩረት ተሠጥቶት እየተሰራ ይገኛል፡፡
በንፍታሌም እንግዳወርቅ
#EBC #ebcdotstream #Ethiopia #Tourism #Heritage UNESCO