በቲክቶክ 2 ሚሊዮን የሚጠጉ ተከታዮች ያሉት ብሩክ ጫላ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን የመጎብኘት ዕድል ማግኘቱን ገልፆ፤ ጉባ ደርሶ ግድቡ ያረፈበትን ቦታ ሲረግጥ የተሰማው ስሜት ልዩ እንደነበር ያስታውሳል።
በዚያ ቅፅበት እኔ የተሰማኝን ኩራት እና ክብር ሁሉም ኢትዮጵያዊ ግድቡን በመጎብኘት እንዲያጣጥመው ምኞቴ ነው ይላል የኢቢሲ መዝናኛ የበዓል እንግዳ የነበረው ቲክቶከር ብሩክ ጫላ።
በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የመካኒካል ኢንጂነርንግ መምህር የሆነው ብሩክ ጫላ በቦታው ላይ ተገኝቶ የግድቡን ግዝፈት ማየት ልዩ ስሜት እንደሚፈጥር ይገልፃል።
ግድቡ ከመመረቁ በፊት በሄደበት ወቅት ሐሩሩን ተቋቁመው በግንባታው ላይ ይሳተፉ የነበሩ ሠራተኞች ጥንካሬ ልዩ ጉልበትን እንደሰጠው ያስታውሳል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ምረቃን ተከትሎ የቲክቶክ ቪዲዮ መሥራቱን የሚናገረው ብሩክ፤ ይህን ተከትሎም በርካቶች ሕዳሴን እንዴት መጎብኘት እንደሚችሉ በአስተያየት መስጫ እንደጠየቁት ይናገራል።
በእኔ ትውልድ ዘመን የተሠራ፣ በኩራት የምናገርለት፣ የኔ ነው የምለው ታሪክ ቢኖር ሕዳሴ ነው የሚለው ብሩክ፤ ሁሉም ቢጎበኘው ምኞቴ ነው ሲል ይገልፃል።
በመሀመድ ፊጣሞ
#EBCdotstream #Ethiopia #GERD