Search

"ቱሪዝምን ለዘላቂ የኢኮኖሚ ሽግግር መጠቀም ይገባል"፦ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ

ቅዳሜ መስከረም 17, 2018 32

ሀገራት ቱሪዝምን ለተፈጥሮ አደጋ የማይበገር የኢኮኖሚ ሽግግር እና ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ መጠቀም እንደሚገባቸው የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ አሳሰቡ።

የዓለም የቱሪዝም ቀን "ቱሪዝም እና ዘላቂ ሽግግር" በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ነው።

ቱሪዝም የሥራ ዕድል በመፍጠር የማኅበረሰብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን ለሀገራት የኢኮኖሚ ዕድገትም ትልቅ አስተዋፅዖ አለው ብለዋል።

በቱሪዝም ሀብቶች አጠቃቀም ያለውን ኢፍትሃዊነት እና የአየር ንብረት ለውጥ እያስከተለው ያለውን ተፅዕኖ በመቀነስ የጋራ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ መሥራት እንደሚገባም አሳስበዋል።

የቱሪዝም ሀብቶችን ለሰዎች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት፣ የምድርን ሚዛን ለመጠበቅ እንዲሁም ልማትን ለማረጋገጥ መጠቀም አስፈላጊ ስለመሆኑ ተገልጿል።

የዓለም የቱሪዝም ተቋም ዳይሬተር አንቶኒዮ ሎፔዝ ባስተላለፉት መልዕክት፥ ሀገራት በዘርፉ ይበልጥ ተጠቃሚ ለመሆን ለትምህርት እና ለፈጠራ ሥራዎች ትኩረት በመስጠት ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

በላሉ ኢታላ

#EBCdotstream #WorldTourismDay #Tourism #SustainableTransformation