የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ የክልሉን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በባህር ዳር መርቀው በይፋ አስጀመሩ።
በማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓቱ የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)፣ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ዓለምአንተ አግደው፣ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ ይርጋ ሲሳይን ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

ማዕከሉ 42 አገልግሎቶችን በአንድ ጣሪያ ስር በማድረግ አገልግሎት የሚሰጥ ነው ተብሏል።
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎቱ ለዜጎች ዘመናዊ እና ቀልጣፋ አገልግሎቶችን ለማቅረብ፣ የአገልግሎት ፈላጊዎችን ጊዜ እና ወጪ ለመቆጠብ እንዲሁም የተገልጋዮችን እርካታ ለማሳደግ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ተመላክቷል።
ማዕከሉ የቢሮ አገልግሎቶችን ከማቅረብ ባለፈም የመኪና ማቆሚያ፣ የሕፃናት ማቆያ እና ሌሎች ዘመናዊ አገልግሎቶችንም አካትቷል።
በሳሙኤል ወርቃየሁ