Search

ትምህርት ሚኒስቴር የሪሜዲያል መግቢያ ነጥብን አሳወቀ

ማክሰኞ መስከረም 27, 2018 141

ትምህርት ሚኒስቴር በ2018 የትምህርት ዘመን በተፈጥሮ እና በማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስኮች ከ49.5 በመቶ በታች አስመዝግበው፤ ነገር ግን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ ተማሪዎች የሪሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ አሳውቋል። በዚህም መሰረት᎓-
1. በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግሥት ተቋማት) የሪሜዲያል ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 33 ከመቶ እና ከዚያ የተቆረጠ መሆኑን።
2. ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግሥት ተቋማት (ወጪያቸው በመንግሥት ተሸፍኖ) የሪሜዲያል ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥቡን ያሟሉ ብቻ ይሆናሉ ብሏል ሚኒስቴሩ።
የመቁረጫ ነጥብ፦
🔥የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 216
🔥የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 204
🔥ታዳጊ ክልል እና አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች
ለሁለቱም ጾታ 198
🔥የማህበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ተማሪዎች ለሁለቱም ጾታ 198
🔥ማህበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ዓይነስውራን ተማሪዎች ለሁለቱም ጾታ 165