በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በጤና ተቋማት ላይ የሚታዩ ችግሮች እዲቀረፉ በትኩረት እንደሚሠራ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ገለጹ።
በክልሉ ጤና ቢሮ ዓመታዊ ጉባዔ ላይ የተገኙት አቶ አሻድሊ፥ ባለፉት ጊዜያት በክልሉ በነበሩ ግጭቶች በእጅጉ የተጎዱ የጤና ተቋማትን መልሶ ለማደራጀት እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
አምራች ዜጋን ለመፍጠር ጤናማ ማኅበረሰብ መገንባት እንደሚያስፈልግ የገለፁት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በክልሉ የጤናውን ዘርፍ ለማሻሻል በትኩረት ይሠራል ብለዋል።
የጤና ተቋማትን የመድኃኒት እና ሌሎች ግብዓቶች አቅርቦት፣ የጤና መድን አገልግሎት እና የጤና ባለሙያዎች አቅምን ለማሻሻል የባለድርሻ አካላት ርብርብ እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ወልተጂ በጋሎ በበኩላቸው፥ 98 በመቶ የሚሆነው የክልሉ ነዋሪ ለወባ በሽታ ተጋላጭ ነው ብለዋል።
በክልሉ የወባ በሽታን ጨምሮ ተላላፊ የሆኑ እና ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከል የተከናወኑ ሥራዎች አበረታች ቢሆኑም፤ ይበልጥ ሊጠናከሩ እንደሚገባም ነው የጠቆሙት።
በነስረዲን ሀሚድ
#ebcdotstream #benshangulgumuz #health