ዓለም አቀፍ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ''ከአደጋ ይልቅ ለአደጋ ስጋት አይበገሬነት ግንባታ ትኩረት እንስጥ'' በሚል መሪ ሃሳብ በተለያዩ መርሃ-ግብሮች እየተከበረ ይገኛል።
የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማሪያም (ዶ/ር) በመርሃ-ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ በኢትዮጵያ በራስ አቅም የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦትን ለመሸፈን የሚረዱ የተለያዩ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።
በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት ለችግር ለተጋለጡ ዜጎች የሚቀርበው ድጋፍም ተጠናክሮ መቀጠሉን አመላክተዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት የካቢኔ ጉዳዮችና የሴክተሮች ክትትል ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አክሊሉ ታደሰ በበኩላቸው፤ በተለያዩ ጊዜያት ያጋጠሙ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎችን ተፅዕኖ ለመቋቋም እና ፈጣን የአደጋ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል የተጠናከረ አቅም እየተገነባ ይገኛል ብለዋል።
በመርሃ-ግብሩ ላይ የፌዴራል እና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች እንዲሁም በአደጋ ስጋት ቅነሳ ላይ የሚሰሩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች ተገኝተዋል።
በሁሴን መሀመድ