Search

ዛሬ የተመረቀው ባለ15 ወለል ዘመናዊው የሲኒማ ማዕከል ለኪነ-ጥበብ ዕድገት አዲስ ምዕራፍ ከፋች ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ማክሰኞ ጥቅምት 04, 2018 34

ዛሬ ያስመረቅነው ባለ 15 ወለል ዘመናዊ የሲኒማ ማዕከል በአይነቱ ልዩ እና ለኪነ-ጥበብ ዕድገት አዲስ ምዕራፍ ከፋች መሆኑን ሳበስር በደስታ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ።
 
መንግሥት የኪነ-ጥበብን ወሳኝ ሚና በመረዳትና ልዩ ትኩረት በመስጠት በቢሊዮኖች በጀት መድቦ በአይነታቸው ልዩና ዘመናዊ ለሲኒማ ፣ለቴአትር ራሳቸውን የቻሉ ትልልቅ ማዕከላትን ሲገነባ ፤ በኪነ-ጥበብ ዘርፈ የተሰማራችሁ ከያኒያንና የጥበብ ቤተሰቦች ሁሉ፣ ለሀገራችን ሁለንተናዊ ብልፅግና መረጋገጥ መሰረት የሚሆኑ የጥበብ ሥራዎችን በማበርከት፣ ታሪክ የማይዘነጋው ዘመን ተሻጋሪ አስተዋጽዖ እንደምታበረክቱ በማመን ነው ብለዋል።