የጋምቤላ ክልል የምግብና ሥርዓተ-ምግብ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ጋር በመተባበር የሥራ አፈፃፀም ግምገማ አካሂዷል።
በወቅቱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ እንዳሉት፤ ያልተስተካከለ ሥርዓተ-ምግብ በተለይም በሴቶችና ሕጻናት ላይ የጤና እክል ከማስከተል አልፎ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር እየፈጠረ ነው።

በመሆኑም በክልሉ ያለውን ሰፊ የእንስሳት እና ዓሣ ሃብት ጥቅም ላይ በማዋል እንዲሁም የግብርና ምርትን በማጠናከር ሥርዓተ-ምግብን ማሻሻል እንደሚገባ አመላክተዋል።
የተመጣጠነ የምግብ አቅርቦት ላይ ሰፊ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚገባም አሳስበዋል።
በሚፍታህ አብዱልቃድር